በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ “መጭው አይታወቅም” - ተንታኞች


ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ቅዳሜና ዕሁድ በተካሄድ የተቃውሞ ሰልፎች የተገደለው ሰው ቁጥር ወደ መቶ እንደሚጠጋ አንዳንድ ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ቅዳሜና ዕሁድ በተካሄድ የተቃውሞ ሰልፎች የተገደለው ሰው ቁጥር ወደ መቶ እንደሚጠጋ አንዳንድ ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መታሠራቸውና ብዙዎች ላይ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል፡፡

ዋና መሥሪያ ቤቱ ለንደን - እንግሊዝ የሆነው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ተሟጋች ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት በቅዳሜና በዕሁዱ የኦሮምያና የአማራ ክልሎች የተቃዋሚ ሰልፈኞችና የመንግሥት ኃይሎች ግጭቶች የጠፋው ሕይወት ዘጠና ሰባት መድረሱን አስታውቋል፡፡

ተቃዋሚዎችና የመብቶች ተሟጋቾች በሚያወጧቸው መግለጫዎች የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ባልታወቀና ድምፃቸውን በሰላማዊ ሁኔታ ሲያሰሙ በነበሩ ሰልፈኞች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን እየተናገሩ ነው፡፡

ከመንግሥቱ ወገን የሚናገሩ የሚሉት ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡

ከተቃዋሚዎቹ ሰልፈኞች መካከል ገዳይ መሣሪያ ወይም ትጥቆችን የያዙ እንደነበሩ አመልክተዋል፡፡

“በፈንጂና በቦምብ በፀጥታ ኃይሎችና በተቋማት ላይ ጥቃት አድርሰዋል፤ ሰልፎቹ የተዘጋጁት በሁከት ኃይሎች ነው፤ ፍቃድም አልተሰጣቸውም” ብለዋል፡፡

ምንም እንኳ በአማራና በኦሮምያ ክልሎች ውስጥ ያሉት ሰልፎች እየተካሄዱ ያሉት በተመሣሣይ ጊዜ ቢሆንም ሰበቦቻቸው ግን የተለያዩ መሆናቸውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአካባቢው የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ፈታሽና መርማሪ ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በኢትዮጵያ “መጭው አይታወቅም” - ተንታኞች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG