በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ለ650 የህግ ታራሚዎች ይቅርታና ምህረት ተደረ


የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

በኢትዮጵያ ለ650 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታና ምህረት ተደርጎ በመፈታት ላይ መሆናቸው ተገለጠ፡፡

በኢትዮጵያ ለ650 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታና ምህረት ተደርጎ በመፈታት ላይ መሆናቸው ተገለጠ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የይቅርታ ቦርድ በሐምሌ 28/2010 ዓ.ም ባሳለፈው የውሳኔ ሀሳብ መሰረት ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ታራሚዎቹ እንዲፈቱ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።

በሀገር ውስጥ ዘገባዎች መሰረት ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች ድሬደዋ፣ ከቃሊቲ፣ ዝዋይ እና ቂሊንጦ ማራሚያ ቤት የሚገኙ ናቸው።

ታራሚዎቹ በይቅርታ አዋጁ መስፈርት መሰረት በልዩ ሁኔታ ማለትም በዕድሜ መግፋት፣ በከባድ ጤና ችግርና የተፈረደባቸውን ፍርድ አንድ ሦስተኛ የጨረሱ እንዲሁም የገንዘብ ቅጣታቸውን የከፈሉ እንደሚገኙባቸው ዘገባው አመልክቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG