በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመሸጥ የሚያስችላትን የማስተላለፊያ መስመር ልትገነባ ነዉ


New Image 1
New Image 1
ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመሸጥ የሚያስችላትን የማስተላለፊያ መስመር ልትገነባ ነዉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:13 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ወደ 120 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣዉን የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ከሚገነባዉ የቻይና ኩባንያ ጋር ተፈርሟል። የግንባታ ስራዉም ስምምነቱ ከተፈረመ ጀምሮ ሶስት ዓመት ከስድስት ወር እንደሚወስድ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ እንጂነር አዜብ አስናቀ ተናግረዋል። እንጂነር አዜብ እንዳብራሩት የማስተላለፊያ መስመሩ አጠቃላይ ርዝመት 1 ሺህ አርባ አምስት ኪሎ ሜትር ነዉ። ከዚህ ዉስጥ በኢትዮጵያ በኩል የሚገነባዉ ከወላይታ ሶዶ ተነስቶ ኬንያ ድንበር የሚደርሰዉ 433 ኪሊ ሜትሮች እርዝማኔ ያለዉ መስመር ነዉ። በወላይታ ሶዶ የሚገነባዉ የማከፋፈያ ጣቢያ ለሌሎች የአፍሪቃና የመካከለኛዉ ምስራቅ አገሮች ሊሸጥ የሚችለዉን የሃይል መጠን ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

ኬንያ ከጂቡቲና ከሱዳን በመቀጠል ኢትዮጵያ የኤልክትሪክ ሃይል የምትሸጥላት ሶስተኛ አገር ትሆናለች ማለት ነዉ። ኬንያና ኢትዮጵያ አንዱ ከሌላዉ ሃይል ለመሸመት ከስምምነት የደረሱት 2006 ዓም መሆኑ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG