በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤተሰብ ምጣኔ የኢትዮጵያ ስኬት


ዩኤንኤፍፒኤ
ዩኤንኤፍፒኤ

ኢትዮጵያ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ በቤተሰብ ምጣኔ አበረታች ውጤት ማስመዝገቧ ተገለፀ፡፡ ይሁንና ብዙ ፈተናዎች እንደተደቀኑ መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

የእናቶችን ሞት በመቀነስ በኩል የሚሌኒየሙን ግብ መምታት በጣም አስቸጋሪ ነው ተብሏል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በታዳጊ ሃገሮች ውስጥ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶችን ለሁሉም እንዲደርሱ ለማድረግ በየዓመቱ ለእናቶችና ለአራስ ሕፃናት የሚውለውን የጤና እንክብካቤ ወጭ በ11.3 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ያደርገዋል፡፡

የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ የሚውለው ገንዘብ እጅግ አስተማማኝ መልዕለ-ነዋይ እንደሆነም መግለጫው ያስረዳል፡፡
ቡንሚ ማኪንዋ፤ የዩኤንኤፍፒኤ የአፍሪካ ሪጅናል ቢሮ ዳይሬክተር
ቡንሚ ማኪንዋ፤ የዩኤንኤፍፒኤ የአፍሪካ ሪጅናል ቢሮ ዳይሬክተር

የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG