አዲስ አበባ —
ዘጠኝ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ”ትብብር ለዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ” በአጭሩ ”ትብብር” የተሰኘ አዲስ የፓርቲዎች ቅንጅት መመሥረቱን ባለፈው ዕሁድ ይፋ አድርገዋል።
ተቃዋሚ ፓርቲዎች አዲስ በተቋቋመው ትብብርና ቀደም ሲል በተመሠረተው መድረክ ውስጥ መሰባሰባቸው አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች ሁለት የተለያዩ ጥምረቶች ውስጥ መግባቸውን አሳይቷል።
በብሔር ከተደራጁ ፓርቲዎች ጋር እንደማይቀናጅ ሲገልፅ የቆየው መኢአድም የአዲሱ ትብብር አባል ሆኗል።
የ2007ቱ ሀገር አቀፍ ምርጫ ከሁለት ዓመታት ያነሰ ጊዜ በቀረው በዚህ ወቅት ግን የተቃዋሚዎች አሰላለፍ “ለይቶለታል” ማለት እንደማይቻል አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ለቪኦኤ ገልፀዋል።
እስክንድር ፍሬው ስለ አዲሱ ትብብር ዓላማና ራዕይ ያገኘውን ምሁራዊ ትንተና አክሎ ዘግቧል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያድምጡ፡፡