በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተመንግሥት ገቡ

  • እስክንድር ፍሬው

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝና ቤተሰባቸው ወደ አራት ኪሎው ቤተመንግሥት ገቡ
አቶ መለስ ዜናዊን በመተካት ከአምስት ሣምንታት በፊት ቃለ መሃላ የፈፀሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝ ወደ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት የታዘወሩት ከትላንትና በስቲያ ዕሁድ ነው።
አቶ ኃይለማሪያም ሥራቸውን ወዲያው የጀመሩት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀላቸው ጊዜአዊ ቢሮ እንደነበር ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ገልፀዋል።
ከሁሉም በላይ ትኩረት ስቦ የቆየው ግን ላለፉት አምስት ሣምንታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመኖሪያ ቤታቸው እየተመላለሱ ለመሥራት መገደዳቸው ነው።
ለዚህም ምክንያቱ የቀድሞዋ ቀዳሚት እመቤት አዜብ መስፍን ቤተመንግሥቱን ለቅቀው አለመውጣት እንደነበረ አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ጠቅሰዋል።
አንድ የኢትዮጵያ መሪ ከቤተመንግሥት ውጭ ሲኖር አቶ ኃይለማሪያም የመጀመሪያው እንደሆኑ በመግለፅ የተቹም ነበሩ።
ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያድምጡ።
XS
SM
MD
LG