አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ ፓርላማ ለመጭው ዓመት ከአንድ መቶ ሰባ ስምንት ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መድቧል።
በወጪ ንግድ የተያዘው ዕቅድ ችግር እንደገጠመው በፓርላማው ተገልጿል።
በሌላ በኩል ከግብፅ ጋር ያለው ግንኙነት የተሻለ አቅጣጫ እንደያዘ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደላለኝ አመልክተዋል።
የሦስትዮሽ የቴክኒክ ኮሚቴ ሥራ እንደሚጀመርም ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡