በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፍትሕና የፍኖተ ነፃነት ሕትመትና የመንግሥትና የአንድነት ሃሣቦች


ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ - የአንድነት ሊቀመንበር /ፎቶ - ከፋይል የተገኘ/
ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ - የአንድነት ሊቀመንበር /ፎቶ - ከፋይል የተገኘ/

“የፍትሕና የፍኖተ ነፃነት ጉዳይ የንግድ ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ፡፡ “የለም፤ ፖለቲካ ነው” - ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ


please wait

No media source currently available

0:00 0:12:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


የፍትሕ ጋዜጣ እና የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ልሣን የሆነችው “ፍኖተ ነፃነት” ጋዜጣ አለመታተም የንግድ እንጂ የአስተዳደር ጉዳይ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ አስታወቁ፡፡ የአንድነት ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ ግን የፖለቲካ ሥውር ክትትልና እርምጃ ውጤት ነው ብለው ያምናሉ፡፡

ፍትሕ ጋዜጣ እና ፍኖተ ነፃነት በአታሚው ብርሃንና ሠላም ድርጅት “አላትምም” ባይነት ምክንያት ለሕዝብ ንባብ ሳይበቁ ቀርተዋል፡፡
ሁኔታው የተነሣበትንና የደረሱበትን የአንድነት ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሦ ጊዳዳ ለቪኦኤ በስልክ ሲያብራሩ ምንም እንኳ ብርሃንና ሠላም ሌሎች ሥራዎችን በጨረታ ስላሸነፍኩ አቅም ስለሌለኝ ነው ቢልም ማተሚያ ቤቱ ጋዜጣቸውን አላትምም ያለው ከመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች በተላለፈ ትዕዛዝ መሠረት መሆኑን እንደሚያውቁ ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም በጉዳዩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ጣልቃ እንዲገባ አቤቱታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለት ተከታታይ ደብዳቤዎች ማሣወቃቸውን ጠቅሰዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ትናንት ለፓርላማው ቀርበው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅትም ይኸው ጉዳይ ተነስቶ ደብዳቤው እንደደረሣቸው ቢያስታውቁም ጉዳዩ የንግድና በመሆኑ ፅ/ቤታቸው በከተማይቱ ውስጥ ለሚገኙ 34 ማተሚያ ቤቶች ይህንን ሥራ ተቀበሉ፤ ይህንን አትቀበሉ የሚልበት እሠራር እንደሌለ ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም ጉዳያቸውን መጨረስ ያለባቸው ከማተሚያ ቤቶቹ ወይም በፍርድ ቤት መሆን እንደሚገባው ተናግረው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ጥያቄአቸውን እንደገና እንዲመረምሩ አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ግን ወደ ብዙ የግል ማተሚያ ቤቶችም ሄደው መሞከራቸውንና አንዳንዶቹ ልሣናቸውን የማተም ሥራውን ለመቀበል ከተዋዋሉና ክፍያም ከወሰዱ በኋላ ሃሣባቸውን እንደሚቀይሩና እንደሚመልሱላቸው ገልፀው ይህንን የሚያደርጉት በፍርሃት ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“ሥውር የፖለቲካ ክትትልና ድብቅ የሣንሱር አድራጎት በመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት” እንደሚካሄድ እንደሚያውቁ ዶ/ር ነጋሶ ገልፀው ቀደም ሲልም ማተሚያ ቤቶች የሕትመት ሥራ ይዘው ከሚሄዱ ደንበኞቻቸው ጋር ሣንሱር የማድረግ አቅም የሚሰጣቸው ውል እንዲፈርሙ ተጠይቀው እንደነበርና ያ ጉዳይም አሁንም አጨቃጫቂ እንደሆነና በእንጥልጥል ላይ እንደሚገኝም አስታውሰዋል፡፡

ሪፖርቱን ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG