በስም መጠቀስ ያልፈለጉ አባቶች ለቪኦኤ እንዳረጋገጡት ከሆነ ይኸው አስመራጭ ኰሚቴ ዕጩ ተወዳዳሪዎችን እስከ ጥር ሰላሣ እንዲያሣውቅ በሲኖዶሱ ተወስኗል።
የኢትዮጵያው ቅዱስ ሲኖዶስ ቀደም ሲል በተጀመረው የዕርቅና የሠላም ድርድር ላይ እንዲገኙ ሦስት አንጋፋ ሊቃነ-ጳጳሣትንና አንድ ካህን የተካተቱበትን ባለ አራት አባላት የልዑካን ቡድን ወደ አሜሪካ መላኩ ይታወሣል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የሲኖዶሱ ዋና ፀሐፊ አቡነ ሕዝቅኤል በወቅቱ ተጠይቀው «አሁን ስብሰባ ላይ ነኝ» በማለት መልስ መስጠት አልፈለጉም።
ይሁንና አንዳንድ የቤተ-ክርስቲያኒቱ አባቶችና ሊቃውንት በተለይም ካዲሳባ ከመጡት የሠላም ልዑካን መካከል ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ ሲኖዶሳቸው የወሰደውን አቋም ተቃውመዋል። ለቪኦኤ በሰጡት ቃልም፣ «ይህ ነገር ይሆናል ብለን አናምንም፣ ከሆነ ግን ትክክል አይደለም፣ እንቃወማለን» ነው ያሉት።
ይህንኑ አቋም ይበልጥ ያስተናገዱት፣ የዋሽንግተን ዲ.ሲ.፣ የቨርጂንያና የሜሪንድ እንዲሁም የካሊፎርኒያ አህጉረ-ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ናቸው። በዚሁ መሠረት «ለቤተ-ክርስትያን ሠላም ይበጃል የምለውን፣ የግሌን» በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተውናል።
ዝርዝሩን ከቃለምልልሱ ያዳምጡ፡፡