በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የመድረክ መግለጫ መንግሥትን ይከስሣል


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በእሥረኞች ላይ የሥቃይ ምርመራ ይፈፀምባቸዋል‘ ሲል መንግሥትን ከሠሠ።

ፀረ-ሽብር ሕጉንም እንደሚቃወምና እንዲሠረዝም እንደሚታገል አስታውቋል።

መድረክ ትናንት ባሠራጨው የፅሁፍ መግለጫ "የኢትዮጵያ ሕዝብ ወራሪዎችና ኮሎኒያሊስቶችን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ የሃገሩን ክብርና ነፃነት ያስጠበቀ ቢሆንም ከራሱ አብራክ የወጡ አምባገነኖች ለሚፈጥሩበት ሁልአቀፍ ችግርና መከራ ግን እስከዛሬ ሁነኛ መፍትሔ ሳያገኝላቸው ቆይቷል" ይላል፡፡

"ሃገራችን ከምንጊዜውም የከፋ የዜጎች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች የሚፈፀሙባት፣ የመደራጀትና ሃሣብን በነፃ የመግለፅ መብቶች የተጣሱባት፣ ነፃ ዳኝነት የጠፋባት ሃገር ሆናለች" ብሏል መግለጫው፡፡

በተለይ ግን በኦሮሚያ ክልል አካባቢ የሚታየው በእጅጉ የከፋ እንደሆነ የመድረክ አመራር አባልና የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና አስረግጠው ይናገራሉ፡፡

ለዚህ የመድረክ ክስ መልስ እንዲሰጡን በኦሮሚያ የአስተዳደርና ደህንነት ቢሮ የሥራ ሂደት፣ የመረጃና ህዝባዊ ግንኙነት ኃላፊ ለአቶ መስፍን አሰፋ ስልክ ደውለን ነበር። እርሣቸውም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝባዊ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አበበ መልስ እንደሚሰጡን ነገሩን። ኮማንደር አበበ ስልካቸውን አይመልሱም። ከኦሮሚያ ክልልና ከፌዴራል መንግሥት ባለስልጣናት ለዚህ የመድረክ መግለጫ መልስ የማግኘት ጥረታችንን እንቀጥላለን።

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG