በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦብነግ ‘የተጠለፉ’ ያላቸው መሪዎቹ ሆስፒታል እንደሚገኙ ገለፀ

የኦብነግ ታጣቂዎች /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የኢንተርኔት ኢንሳይክሎፔድያ የተገኘ/የኦብነግ ታጣቂዎች /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የኢንተርኔት ኢንሳይክሎፔድያ የተገኘ/
የኦብነግ ታጣቂዎች /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የኢንተርኔት ኢንሳይክሎፔድያ የተገኘ/የኦብነግ ታጣቂዎች /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የኢንተርኔት ኢንሳይክሎፔድያ የተገኘ/

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር - ኦብነግ በቅርቡ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ “ተጠልፈውብኛል” ባላቸው ሁለት ከፍተኛ የአመራር አባላቱ ላይ ድብደባና የሥቃይ አያያዝ መድረሱን ግንባሩ አስታውቋል፡፡
የኦብነግ አርማ /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የኢንተርኔት ኢንሳይክሎፔድያ የተገኘ/
የኦብነግ አርማ /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የኢንተርኔት ኢንሳይክሎፔድያ የተገኘ/

please wait

No media source currently available

0:00 0:22:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር - ኦብነግ በቅርቡ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ “ተጠልፈውብኛል” ባላቸው ሁለት ከፍተኛ የአመራር አባላቱ ላይ ድብደባና የሥቃይ አያያዝ መድረሱን ግንባሩ አስታውቋል፡፡

ግለሰቦቹ “በጠለፋው ወቅት ደርሶባቸዋል” ባለው ድብደባ ምክንያት በመቁሰላቸው በሁለት ሆስፒታሎች ውስጥ እየታከሙ መሆናቸውንም ግንባሩ ትናንት የካቲት 3/2006 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

ኦብነግ “የኦጋዴን ብሔራዊ ባንዲራ” የሚለው ባንዲራ /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የኢንተርኔት ኢንሳይክሎፔድያ የተገኘ/
ኦብነግ “የኦጋዴን ብሔራዊ ባንዲራ” የሚለው ባንዲራ /ፎቶ - ከዊኪፔድያ የኢንተርኔት ኢንሳይክሎፔድያ የተገኘ/
የግንባሩ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “የኢትዮጵያ መንግሥት ቀደም ባሉ ግዜያትም የሰላም ስምምነቶችን ከግለሰቦች ጋር ተፈራርሜአለሁ እያለ የፈጠራ ስምምነቶችን ይፈርም ነበር” ብለዋል፡፡

ትናንት የወጣው የግንባሩ መግለጫ “እነዚያን ሰዎች አንድም በማስገደድ፣ አልያም በተጋነነ የሃብትና የሥልጣን ዳረጎ በማማለል የሃቀኛ ነፃ አውጭ ግንባሮችን እና ተቃዋሚዎችን ተዓማኒነት ለማሳጣትና ዓለምአቀፉን ማኅበረሰብ በተሣሣተ አቅጣላ ለመምራት ሲጥር ታይቷል” ብሏል፡፡

ተጠልፈዋል የተባሉትን ሰዎች አስመልክቶ ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ወደ ኢትዮጵያ በፈቃዳቸው የገቡ ሁለት የኦጋዴን ተወላጆች መኖራቸውን መስማታቸውንና የሶማሌ ክልል መንግሥትም በጉዳዩ ላይ በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጡ ገልፀው ሌላ የሚያውቁት ዝርዝር መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

የዚህን ዘገባ ዝርዝር እና ከኦብነግ ቃል አቀባይ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ጋር የተደረጉ የኦብነግን የዛሬ አቋምና ፍላጎት የሚያብራሩ ቃለ ምልልሶችን ለመስማት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG