በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ፣ የትራንስፖርት አሰሪዎች ፈደሬሽን ተቃወመው


የትራንስፖርት አሰሪዎች ፈደሬሽን ተቃወመው
የትራንስፖርት አሰሪዎች ፈደሬሽን ተቃወመው
መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ፣ የትራንስፖርት አሰሪዎች ፈደሬሽን ተቃወመው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:33 0:00

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የአገልግሎት ዘመናቸው ከ 30 አመት በላይ የሆኑ ተሽከርካሪዎች፣ ወደ ጅቡቲ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዳይሰጡ ያሳለፈው ውሳኔ ተቃውሞ ገጠመው፡፡ የኢትዮጵያ የትራንስፖርት አሰሪዎች ፈደሬሽን፣ መንግስት ከአንድ አመት በፊት ያወጣውን መመሪያ መሰረት በማድረግ፣ በቅርቡ ከ 30 አመት በላይ የሰሩ ተሽከርካሪዎች ድንበር ተሻጋሪ የጭነት አገልግሎት እንዳይሰጡ ማገዱን ገልፆ፣ ውሳኔው የተለያዩ ችግሮችን ስለሚያስከትል እንደገና ሊጤን ይገባል በማለት ጠይቋል፡፡

ስለ ጉዳዩ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት፣ የፈደሬሽኑ ፕረዝደንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጉዳዩን ዳግም የማይመለከተው ከሆነ፣ አቤቱታችንን ለሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እናቀርባለን ብለዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙርያ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ ምላሽና አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለዛሬ አልተሳካም፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG