በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምክር ቤቱ “የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” 12ኛ የፌዴሬሽኑ አባል ኾኖ እንዲደራጅ ወሰነ


ምክር ቤቱ “የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” 12ኛ የፌዴሬሽኑ አባል ኾኖ እንዲደራጅ ወሰነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:42 0:00

የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት፥ በደቡብ ክልል የሚገኙ፣ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች፣ “የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል” በሚል፣ 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲዳራጅ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ሥር የነበሩት እነዚኽ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች፣ በሁለት ዙር ባካሔዱት ሕዝበ ውሳኔ፣ በአንድ የጋራ ክልል የመደራጀት ፍላጎታቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን አስታውቋል።

“የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል” በሚል በዐዲስ እንዲደራጁ የተወሰነው፥ የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የጌዴኦ፣ የደቡብ ኦሞ፣ የኮንሶ ዞኖች እና የደራሼ፣ የቡርጂ፣ የአማሮ፣ የኧሌና የባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች ናቸው፡፡

በቀድሞ የደቡብ ክልል ውስጥ የነበሩ፥ የሀድያ፣ የሀላባ፣ የከምባታ ጠምባሮ፣ የስልጤ፣ የጉራጌ ዞኖች እና የየም ልዩ ወረዳ ደግሞ፣ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በሚል እንደሚቀጥሉ ምክር ቤቱ አስታውቋል።

ቪኦኤ ያነጋገራቸው፣ የፖለቲካ ሳይንስ እና የሕግ ምሁራን፥ የደቡብ ክልል ህልውናውን ማጣቱን ጠቅሰው፣ ክልሉ እንዲፈርስ ምክንያት ናቸው ያሏቸው የፍትሐዊነት፥ የልማት እና የመልካም አስተዳደር፣ እንዲሁም የፖለቲካ ውክልና ጥያቄዎችን፣ አሁንም ትኩረት እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።

የወላይታ ሕዝብ ብሔራዊ ንቅናቄ በበኩሉ፣ ውሳኔው፥ የአንድ ወገን የበላይነት የተንጸባረቀበት ነው፤ ሲል ውሳኔውን እንደማይቀበል ገልጾ ኮንኗል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG