የአዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አስተዳደር ምን ዓይነት መልክ ይኖረዋል? በሃገር ውስጥ፥ በተለይ በፖለቲካው፥ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ፥ እንዲሁም የመገናኛ ብዙኃንና የንግግር ነጻነት ከበሬታን አስመልክቶስ ምን ዓይነት ፖሊሲዎችን ያራምድ ይሆን?
የጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን አስተዳደርና አገሪቱ በአስተዳደር ዘመናቸው ልትከተል የምትችለውን አቅጣጫዎች አስመልክቶ የተሰነዘሩ የሁለት ወገን እይታዎች ዛሬም ከክርክሩ መድረኩ ተሰይመዋል።
የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች፥ የኢትዮጵያን መንግስት ፖሊሲዎች በመደገፍ የሚከራከሩት፥ አቶ መኮንን ካሳ ከዚህ ከዩናይትድ ስቴትስ፤ የመንግስቱን ፖሊሲዎች በመቃወም የተከራከሩት፤ አቶ መስፍን አማን ናቸው፤ ከሆላንድ፥ አምስተርዳም።