የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም በድጋሚ ጥሪ ያቀረቡት በጉዳዩ ላይ ከተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዚዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ ጋር መወያየታቸውን በገለጹበት በዛሬው የትዊተር መልዕክታቸው ነው፡፡
ይሁን እንጂ ስለውይይታቸው ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም፡፡ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ ያለው የሠላም ንግግር ዛሬ ለ3ተኛ ቀን ቀጥሏል። ሆኖም በንግግሩ ስለተነሱ ጉዳዮች ከየትኛውም ወገን መረጃ አልተሰጠም፡፡