የኢትዮጵያ መንግሥት ሐሙስ ዕለቱ ባወጣው መግለጫ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ሁከት ለመፍጠር እየሞከሩ ናቸው ለሚላቸው ወገኖች ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን እንዲያከብሩ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡
በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ በተለይ የአወሊያን ትምህርት ቤትና አንዳንድ ያላቸውን መስጊዶች በስም ይጠቅሣል፡፡
የሕዝበ ሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሣቢ አቡበከር አህመድ በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ስለወጣው መግለጫ ከቪኦኤ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል፡፡
ዝርዝሩን ያድምጡ