አዲስ አበባ —
ለአለፉት አሥር ወራት ተጥሎ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ፡፡
“አዋጁ እንዲታወጅ መነሻ የነበሩ ሁኔታዎች በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንሱ ተደርገዋል” ብሏል፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፓስት ሲክሬታርያትና የመከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሣ፡፡
ሁከት፣ ብጥብጥ፣ ሽብር በመፍጠር ወንጀል የተጠረጠሩ ሰባት ሺሕ ሰባት መቶ ሠላሳ ሰባት ሰዎች ግን አሁንም በእሥር ላይ አንደሚገኙና በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ክሳቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
አንጋፋው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ግን፣ አዋጁ መታወጅም ሆነ ለአሥር ወራት መቆየት አልነበረበትም ብለዋል፡፡
“የፍርኃትና የተፅዕኖ ድባብ፣ በሀገሪቱ ያሰፈነ ነበር” ሲሉም ነው የገለፁት፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ