ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
ካሩቱሪ ግሎባል ኢትዮጵያ ውስጥ ሰፋፊ መሬቶችን በኪራይ ወስዶ አበባና ሰብሎችን እያመረተ የሚገኝ ግዙፍ አግሮ ኢንዱስትሪ ኩባንያ ነው፡፡

ኩባንያው ኢትዮጵያ ውስጥ በጋምቤላ ክልል ከ200 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ተረክቦ እየሠራ ሲሆን ኦሮሚያ ውስጥም በባኮ ከተማ አቅራቢያ በቅርቡ እንዲሁ ሰፊ የእርሻ ማሣ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
ካሩቱሪ ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ የጀመረው የዛሬ 18 ዓመት አበባ ወደ ውጭ በመላክ ሲሆን አሁንም በዚሁ ሥራው እንደሚቀጥል የካሩቱሪ ግሎባል መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ካሩቱሪ ግሎባል ዛሬ መሪው የአበባ አምራችና ላኪ መሆኑንና እስከአሁንም ከግማሽ ቢሊየን በላይ እግር አበባ ከኢትዮጵያና ከኬንያ ምርቶቹ ለውጭ ገበያ መላኩን ሚስተር ካሩቱሪ አስታውቀው በአበባ ምርትና ገበያ ኢንቨስትመንታቸው ላይ ሰባት ሺህ የሚሆን ሰው እየሠራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የዛሬ ሦስት ዓመት አባባቢ ደግሞ በሌሎች የግብርና ምርቶች ላይ ለመሠማራት አስበው ከኢትዮጵየ መንግሥት መሬት ተከራይተው እየሠሩ መሆናቸውን፣ ሩዝ፣ በቆሎ፣ የዘንባባ ዘይትና የሸንኮራ አገዳ ለማልማት መሬቱን እያዘጋጁ መቆየታቸውን፣ ባለፈው ዓመትም የመጀመሪያ ምርታቸውን በአጥጋቢ ሁኔታ ማንሣታቸውን ገልፀዋል፡፡
የካሩቱሪ ግሎባልን ኢንቨስትመንት፣ የመሬት ኪራይና ነጠቃን ጉዳይ እሰጥ አገባ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት አቋምና በተቃዋሚዎች መካከል ያለውን ልዩነት የሚዳስሰውን ዘገባ ለተጨማሪ መረጃ ያዳምጡ፡፡