አዲስ አበባ —
ፖሊስ “አመፅ በመቀስቀስ ጠርጥሬአቸዋለሁ” ብሎ ከሦስት ሣምንታት በፊት ከያዛቸው ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት አምደኞች (ብሎገሮች) መካከል አንዳንዶቹ “ድብደባና ሌላም ሌላም ሥቃይ ደርሶብናል” ሲሉ ለፍርድ ቤት ተናገሩ፡፡
ፖሊስ በበኩሉ ምርመራውን በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት ለማጠናቀቅ ሃያ ስምንት ተጨማሪ ቀናት ጠይቋል፡፡
ጠበቆች ጥያቄውን ቢቃወሙም ፍርድ ቤቱ ግን ከፖሊስ የቀረበውን ጥያቄ ተቀብሎ የጊዜ ቀጠሮውን አፅድቋል፡፡
ለዝርዝሩ የመለስካቸው አምሃን ዘገባ የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡