አዲስ አበባ —
በነሶሊያና ሺመልስ የክስ መዝገብ በተከሰሱት ጋዜጠኛችና የኢንተርኔት አምደኞች ላይ አቃቤ ሕግ ከቆጠራቸው ምስክሮች ዛሬ ተሰሙ፡፡
ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ተከሳሾቹ የአቶ ሌንጮ ለታን የፖለቲካ ድርጅት ማኒፌስቶ በኮምፕዩተሮቻቸው ውስጥ እንደተገኙ መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
ሌሎች ደግሞ ተከሣሾቹ ቢሮም ሆነ መኖሪያ ቤት ከገበያ ላይ የሚገዙ መፅሔቶችና ጋዜጦችን እንደተመለከቱ ለፍርድ ቤት ገልፀዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን የችሎት ዘገባ ያዳምጡ፡፡