በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጂማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄ፣ የአስተዳደሩና የኅብረታቸው ምላሽ


ጂማ ዩኒቨርሲቲ
ጂማ ዩኒቨርሲቲ

ጂማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ትናንት ተፈጥሯል በተባለ ችግር ከፖሊስ ጋር ግጭት እንደነበረ አንዳንድ ተማሪዎች ሲገልፁ የተፈጠረ ግጭትም ይሁን የተጎዳ ተማሪ አለመኖሩን የተማሪዎቹ ኅብረት ፕሬዚዳንት እና የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ለቪኦኤ ገለፁ፡፡




please wait

No media source currently available

0:00 0:19:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የተማሪዎቹ አድማ የተጀመረው የሚፆሙ ተማሪዎች ባቀረቡት የዳቦ ጥያቄ እንደነበረ አንዲት የዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ሣይንስ ክፍል የሁለተኛ ዓመት ተማሪ መሆኗን የተናገረች ወጣት ገልፃለች፡፡

ጂማ ዩኒቨርሲቲ
ጂማ ዩኒቨርሲቲ

ተማሪዎቹ በፆሙ ምክንያት “የሚቀርብልን ዳቦ መጠን ይጨመርልን፣ የሚቀርቡትን ቅንጬና የመሣሰሉ ቅቤ የሚገባባቸውን ምግቦች እንደማይጠቀሙ አመልክተው ተጨማሪ ዳቦ እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ፡፡

ያ ጥያቄአቸው እስኪመለስም ከነበሩበት የመመገቢያ አዳራሽ እንደማይወጡ በመግለፃቸው ፖሊስ ተጠርቶ መግባቱንና በተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልፃለች፡፡

የግቢው ሁኔታ ዛሬ የተረጋጋ መሆኑንና ተማሪዎቹ ወደ ትምህርታቸው መመለሣቸውንም ተናግራለች፡፡

ስለሁኔታው መግለጫ የሰጠን የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዚዳንት ዳዊት ጌታቸውም ያመፁት ተማሪዎች ጥያቄ አግባብነት የለውም ብሎ እንደማያምን ይሁን እንጂ ጥያቄአቸውን ያቀረቡት አግባብነት ባለው መንገድና ሁኔታ እንዳልሆነ ገልፆ ጥያቄአቸውን ለማየት ጥረት መደረጉን አመልክቷል፡፡

ተማሪዎቹ ከመመገቢያ አዳራሹ ለመውጣት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት ፌደራል ፖሊስ ወደግቢው እንዲገባ መደረጉ ትክክል ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል፡፡ ተማሪዎቹ ሙሉ በሙሉ ሠላማዊ እንደነበሩ፣ ያጠፉት ንብረትም ሆነ የጎዱት ሰው አለመኖሩግ ዳዊት ጠቅሶ በተማሪዎቹ እና በፖሊሶቹ መካከል ግን ግጭት አለመፈጠሩን፤ የተጎዳ ተማሪም እንደሌለ ተናግሯል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የሥርዓተ-ትምህርት፣ የምርምርና የተማሪዎች ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ዶ/ር ታየ ቶለማርያም ተማሪዎቹ ያነሷቸውን ጥያቄዎች ወዲያውኑ ለመፍታት እንደሚያስቸግር፣ ምግብ የሚቀርበው በጨረታ ከሚያሸንፍ ድርጅት በመሆኑ ጊዜ እንደሚወስድ ተነግሯቸው ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ መጠየቃቸውንና ተማሪዎቹ ለመመለስ ፍቃደኞች ሳይሆኑ መቅረታቸውን ገልፀዋል፡፡

አምስት ሺህ የሚሆኑ ሌሎች ተማሪዎችም መመገብ ስለነበረባቸው አዳራሹን ለማስለቀቅ የውጭ የፖሊስ ኃይል መጋበዛቸውን ደ/ር ታየ አመልክተዋል፡፡ የግቢው የፀጥታ ኃይል ቢኖርም ሁኔታው ከአቅሙ በላይ ነበር ብለዋል፡፡

“በተሰጣቸው ምላሽ ያልተደሰቱት ተማሪዎች፤ ከውጭ የተቀላቀሏቸውም ሊኖሩ ይችላሉ፤ ከዚያ ወጥተው በመኖሪያቸው አካባቢ ባሉ ሕንፃዎች ላይ ድንጋይ ወርውረዋል፣ መስኮቶችንና በሮችንም ሰብረዋል” ብለዋል ዶ/ር ታየ፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
ጂማ ዩኒቨርሲቲ
ጂማ ዩኒቨርሲቲ
XS
SM
MD
LG