በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ሽመና በዓለም አቀፍ ኤግዚቢሺን ላይ እየታየ ነው


የሳሌም ዲዛይን ባለቤት ሳሌም ካሳሁን
የሳሌም ዲዛይን ባለቤት ሳሌም ካሳሁን

“የሀገራችን ሸማኔዎች የእጅ ጥበብ መዳበርና መጠበቅ አለበት” ሲሉ የሳሌም ዲዛይን ባለቤት ሳሌም ካሣሁን አሳሰቡ።

አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ በተከፈተው “ኦሪጂን አፍሪካ - 2015” የሚባል የጥጥ፣ የጨርቃ ጨርቅና አልባሣት ኢንደስትሪ ኤግዚቢሺን ላይ እየተሣተፉ ካሉት በዘርፉ የተሠማሩ ባለድርጅቶች አንዷ ወይዘሮ ሳሌም ካሣሁን ይባላሉ። ወይዘሮ ሳሌም ከባለቤታቸው ጋር ሆነው “ሳሌም ዲዛይን” የተባለውን ድርጅት የመሠረቱ ሥራ ፈጣሪ ናቸው።

“ሳሌም ዲዛይንን ስናቋቋቁም ዓላማችን የነበረው ኢትዮጵያ ብዙ ጥሩ ጥሩ የእደ-ጥበብ ውጤቶች ያሏት ሀገር ሆና ሳለ ያንን ኃብቷን ከጓዳ ወጥቶ ዓለም አላወቀውም፤ እንዲህ ባሉ አደባባዮች ቢታይ ግን ከሌሎች ጋር መወዳደርና መላቅ የሚችል የእደ-ጥበብ ኃብት እንዳለን ስላመንን ነው” ብለዋል።

የሀገራችን ሸማኔዎች የእጅ ጥበብ መዳበርና መጠበቅ አለበት
የሳሌም ዲዛይን ባለቤት ሳሌም ካሣሁን

​ወ/ሮ ሳሌም አክለውም ከዓላማዎቻቸው አንዱም በእደ-ጥበብ ሥራ ላይ የተሠማሩ ባለሙያዎችም ገቢ እንዲያገኙ በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የባህላዊ ሽመና ጥበብ ሰፋ ብሎ እንዲያድግ ድርጅታቸው ምን እየሠራ እንደሆነ የተጠየቁት ወ/ሮ ሳሌም “በኔ እምነት አንድ ሸማኔ በእጁ ሲሠራ፤ ጥበብን ከአዕምሮው እያወጣ በእጁ እየለቀመ ሲሠራ ሙያው ያለው ራሱ ውስጥ ነው። ያ በመኪና /በማሺን/ ከተተካ ጥበቡ ይጠፋል። የሽመና ጥበብ ባለሙያው ያለውን አዕምሯዊ ሥጦታ ማዳበር እንጂ መተካት የለብንም” ብለዋል።

ሙሉውን ውይይት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የኢትዮጵያ ሽመና በዓለም አቀፍ ኤግዚቢሺን ላይ እየታየ ነው /ርዝመት -5ደ44ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:43 0:00

XS
SM
MD
LG