በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ያለፈው ዓመት የዋጋ ንረት እና ውስብስብ መንስዔዎቹ


ያለፈው ዓመት የዋጋ ንረት እና ውስብስብ መንስዔዎቹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:03 0:00

ያለፈው ዓመት 2014 አስቀድሞ ከነበሩት ዓመታት አንጻር ሲታይ በርካታ ኢትዮጵያውያን በኑሮ ውድነት የተፈተኑበት መሆኑን ይናገራሉ። ይህንን አስመልክቶ የተሰሩ ጥናቶችም የዋጋ ንረት ከፍተኛ መሆኑን ያመለክታሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች የምርታማነት አለመጨመር፣ ጦርነት፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲሁም የማስፈጸም አቅሙ የጠነከረ መንግሥታዊ ተቋማትን መገንባት አለመቻል የችግሮች መንስኤ ናቸው ይላሉ።

መንግሥትም የኑሮ ውድነቱን ተጽዕኖ ለመቀነስ ልዩ ልዩ እርምጃዎችን እየወሰድኩ ነው ይላል። ሆኖም ነዋሪዎች እና የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች እርምጃዎቹ ዘላቂ መፍትኄ ያስገኙ አይደሉም ባይ ናቸው።

የዋጋ ግሽበት፣ ጦርነት እና ድርቅን ጨምሮ በኑሮ ውድነት ላይ የደቀኑትን ፈተና በመዳሰስ የድሬዳዋ ዘገቢያችን ያሰናዳውን ዝግጅት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያግኙ።

XS
SM
MD
LG