በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግጭቶች የዋጋ ግሽበቱን ማባባሳቸውን የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማኅበር አስታወቀ


ግጭቶች የዋጋ ግሽበቱን ማባባሳቸውን የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማኅበር አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:48 0:00

የሀገር ውስጥና የውጭ ግጭቶች በኢትዮጵያ ለተከሰተው የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማኅበር አስታወቀ። ማኅበሩ የዋጋ ግሽበትና የፖሊሲ አማራጮችን በተመለከተ ያደረገውን ጥናት ይፋ ባደረገበት ወቅት፣ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ግጭቶች በከፍተኛ መጠን እየጨመሩ፣ በ2021 ብቻ ከ1500 በላይ ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ግጭቶች እንደነበሩ አስታውቋል፡፡ ይህም ለዋጋ ግሽበት ጉልህ አስተዋጽኦ ካበረከቱ ዋነኛ ችግሮች መካከል መሆኑን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን የጥናትና ምርምር ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ደግዬ ጎሹ ገልጸዋል፡፡

ከውጭ ደግሞ የሩሲያና ዩክሬን ግጭት በሀገሪቱ ያለው የዋጋ ግሽበት በፍጥነት እንዲባባስ ማድረጉን የአሶሴሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፕሮፌሰር መንግስቱ ከተማ አብራርተዋል፡፡

አሶሴሽኑ የዋጋ ግሽበትን ለመቅረፍ ያስችላሉ ያላቸውን የመፍትሔ እርምጃዎችንም በጥናቱ ጠቁሟል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG