በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


The Setting Sun of Great Rift Valley
The Setting Sun of Great Rift Valley

ኢትዮጵያ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን በሳምንቱ ውስጥ ስለ ኢትዮጵያ የተጻፉ የተወሰኑ ጽሁፎችን ጨምቆ ያቀርባል።

Christian Science Monitor ጋዜጣ Wlliam Davidson በደቡብ አሞ ተዘዋውሮ ያቀረበውን ዘገባ አስፍሯል። መንግስት በአከባቢው ትልቅ የስኳር አገዳ ተክል ለማልማት ያለውን እቅድ በሚመለከት አንድ ሙርሲ የአከባቢው ተወላጅ እንደሚቃወሙ ሲገልጹ “እኛ ሙርሲዎች የመንግስትን እምነት አንቀበልም" ብለዋል ይላል።

ሰውየው ይህን ያሉት በፍላጎታቸው ከአከባቢው ለመውጣት ለሚስማሙት ሰዎች አዲስ መንደር እንደሚገነባላቸው መንግስት የገባውን ቃል በሚመለከት ነው። እኛ የምንፈልገው በለመድነው ባህላዊ ዘዴ ማምረቱን ነው ሲሉም እንዳከሉበት ክርስችያን ሳይንሳ ሞኒተር ጋዜጣ ላይ የወጣው ጽሁፍ ያወሳል።

የኢትዮጵያ ባለስልጣኖች ሙርሲዎችና ሌሎች በሀገሪቱ ያሉ ጎሳዎች ከጥንታዊው መኖርያቸው በሌሎች መንድሮች ለመስፈር የሚሄዱት በፍላጎታቸው ነው ይላሉ። የሰብአዊ መብት ቡድኖች ግን ልክ አይደለም ሲሉ ይነቅፋሉ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የአፋር ስምጥ መሬት አፍሪቃን የሚከፋፍል አዲስ ውቅያኖስ የመፈጠር ምልክት የሚያሳዩ ትልልቅ ጥልቅ የውሀ ስንጥቆች እንደሚገኙበት የሳይንስ ጠቢባን ይናገራሉ ሲል የሀፊንግተን ፖስት ጋዜጣ ድረ-ገጽ ዘግቧል። ሙሉውን ቅንብር ያድምጡ።

Ethiopia-Press-Review-9-20-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG