በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


ኢትዮጵያ በጋዜጦች የተሰኘው ሳምንታዊ ፕሮግራማችን በሳምንቱ ውስጥ ስለ ኢትዮጵያ የተጻፉ የተወሰኑ ጽሁፎችን ጨምቆ ያቀርባል። የኢትዮጵያው አራቢካ ቡና በ 70 አመታት ጊዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል የሚገልጽ ዘገባ ይገኝበታል።


አራቢካ የተባለው ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የመነጨው ወፍ ዘረሽ የቡና አይነት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ብቻ የያዝነው ምዕተ-አመት ከማብቃቱ በፊት ከገፀ-ምድር ሊጠፋ እንደሚችል የብሪታንያ ሮያል ቦታኒክ ጋርደንስ የሳይንስ ጠቢባን ከኢትዮጵያ የሳይንስ ምሁራን ጋር በመተባበር ባካሄዱት ጥናት እንዳስገነዛቡ EurekAlert የተባለው ስለ ሳይንስ ጤናና ቴክኖሎጂ ጽሁፎችን የሚያቀርብ ድረ-ገጽ ዘግቧል።

በወፍ ዘራሽነት የጀመረው አራቢካ ቡና የተለያዩ የዘረ-መል ይዘቶች ስላሉት ለቡና ኢንዱስትሪ ህልውና ወሳኝ ተደርጎ እንደሚታይ ድረ-ገጹ ጠቁሟል። በአለም የቡና ተክሎች የሚበቅሉት የቡና ዝርያዎች የዘረ-መል አይነት ውሱን በመሆኑ የአየር ለውጥን እንዲሁም ተባይን፣ በሽታንና ሌሎች አደጋዎችን ለመቋቋም የሚያስችል ብቃት እንደማይኖራቸው EurekAlert ጠቅሷል። የአየር ንብረት ለውጥ ከአፍሪቃ ትልቅዋ የቡና አምራች በሆነቸው ኢትዮጵያ የቡና ምርት ላይም አሉታዊ ጫና ሊያሳድር ይችላል።

አራቢካ በአየር ለውጥ ምክንያት ሊጎዳ እንደሚችል ስለተረጋገጠ የአየር ንብረት ለውጥ በአለም ደረጃ ለንግድ በሚመረተው ቡና ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላላ የሚለውን ግምት ያረጋግጣል። ይህ ዘገባ ከነዳጅ ዘይት ቀጥሎ በአለም ደረጃ በሰፈው በሚዘዋወረውና ለአንዳንድ ሀገሮች ኢኮኖሚ ወሳኝ በሆነው የንግድ ቡና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው ድረ-ገጹ አውስቷል።
AMH-af-Ethiopia-Press-Review-11-16-12
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG