በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት ተፅኖ ያሳረበት የኢትዮጵያ የአበባ፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ ገበያ


የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት ተፅኖ ያሳረበት የኢትዮጵያ የአበባ፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ ገበያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:15 0:00

በዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ያልተበገረው የኢትዮጵያ የአበባ፣ የአትክልት፣ የፍራፍሬ፣ የህጸ ጣዕምና የመሰል ምርቶች ውጭ ንግድ በዩክሬን እና ራሺያ ጦርነት ግን ተፅኖ እንዳረፈበት የኢትዮጵያ ሆልቲካልቸር አምራች ላኪዎች ማኅበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ሰዎች በቤታቸው ቁጭ ብለው አበባ የማዘዝና ፍራፍሬ የመመገብ ክፍተኛ ልምድ ስለነበራቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ ሽያጭ ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል።

በሁለት ዓመት ውስጥ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር የሚሆን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ወደ ሃገር ውስጥ ገብቶ እንደነበር ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ሆኖም አሁን ጦርነቱ ከፍተኛ ተፅኖ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG