አዲስ አበባ —
በአዲስ አበባው የንግሥት ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ዛሬ ተመርቆ የተከፈተው የኤችአይቪ/ኤድስ ሕክምና መስጫ ክሊኒክ ለሌሎችም ክሊኒኮችም ምሣሌ የሚሆኑ ተሞክሮዎች እንዳሉት ተነግሯል፡፡
ዛሬ በኢትዮጵያ ለኤችአይቪ ከሚጋለጡ ሰዎች ይልቅ የሕክምና እርዳታ የሚያገኙት ቁጥር መብለጡን አንድ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ባለሥልጣን ተናግረዋል፡፡
ክሊኒኩን ለመገንባት ከ56 ሚሊየን ብር በላይ መፍሰሱና ወጭው የተሸፈነውም በአሜሪካ መንግሥት መሆኑ ታውቋል፡፡
ክሊኒኩን መርቀው የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሣና በዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ ኤድስ መርኃግብር አስተባባሪ አምባሣደር ኤሪክ ጉስፒ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በኤድስ ምክንያት የሚሞተው ሰው ቁጥር በግማሽ መቀነሱን የገለፁትም በኢትዮጵያ የዓለምአቀፉ መርኃግብር አስተባባሪ አምባሣደር ጉስፒ ናቸው፡፡
ለተጨማሪና ዝርዝር የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡