በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኃይለማርያም ደሣለኝ ማን ናቸው?


አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ
አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ

አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ ቃለመሃላ የሚፈፅሙበት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ለፊታችን ዓርብ ተጠርቷል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:12:12 0:00
ቀጥተኛ መገናኛምክር ቤቱ የሚሰበሰው በመደበኛ የመክፈቻ ጊዜው፣ ማለትም በመስከረም መጨረሻ እንደሆነ ሲገለፅ የቆየና የመንግሥት የኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር በረከት ስምዖን ባለፈው ቅዳሜ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፓርላማውን በአስቸኳይ መሰብሰብ አስፈላጊ እንዳልሆነ ገልፀው እንደነበረ የሚታወስ ቢሆንም ይህ ሃሣብ ግን ትናንት ተቀይሮ ስብሰባው በአስቸኳይ እንዲጠራ ስለተወሰነበት ምክንያት የተሰጠ ማብራሪያ የለም፡፡

ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ የኢሕአዴግን ምክር ቤት ሙሉ ድጋፍ ያገኙት አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ “ለኃላፊነቱ በቂ ዝግጅት ያላቸውና መልካም ሰብዕናም የተላበሱ ናቸው” ሲሉ በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡

ለመሆኑ አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ ማን ናቸው? የትምህርት፣ የሥራና የቤተሰባቸውን ጨምሮ የግል ሕይወታቸውን የእስክንድር ፍሬው ዘገባ ይዳስሣል፡፡

የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን መለስካቸው አመሃ ደግሞ በዚሁ በአዲሶቹ የኢሕአዴግና የኢትዮጵያም መሪዎች ላይ አንድ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ስሜት ለመቃኘት ሞክሯል።

ዘገባዎቹን ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG