በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የፊታችን አርብ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ


አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:18 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ሃይለማሪያም ደሳለኝ እስካሁንም በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን የሚጠሩት በዚሁ ማእረግ ነው።
በተለይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩበት ቀን ጀምሮ ሀገሪቷን የመምራት ሃላፊነት ተረክበዋል ቢባልም የመጠሪያቸው ነገር አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል።
ቃለ መሃላ ፈጽመው ሙሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑትም ፓርላማው በመደበኛው ጊዜው በሚያደርገው ስብሰባ እንደሆነ ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።
አቶ ሃይለማሪያም ፓርላማ ቀርበው ቃለ መሃላ እንዲፈጽሙ የማድረጉ ጉዳይ አስቸኳይ እንዳልሆነም በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ የተገለጸው በተደጋጋሚ ነው።
ባለፉት ሁለት ቀናት ግን ያልተጠበቀና ድንገተኛ ጥሪ ለፓርላማ አባላት ተላልፎአል። እናም የፊታችን አርብ በሚያደርገው አስቸኳይ ስብስባ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቃለ መሃላውን እንደሚፈጽሙ ይጠበቃል።
ስነስርዓቱ በድንገት እንዲከናወን የተወሰነውም የፊታችን ማክሰኞ በሚከፈተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ አገሪቱን ወክለው እንዲገኙ መሆኑ ተጠቁሞአል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከኢህአዴግ አራት አባል ድርጅቶች አንዱ የሆነው ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በሊቀመንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ሞት የተፈጠረውን የስልጣን ክፍተት ለመድፈን ምርጫ አካሂዷል።
በዚሁ ፓርቲ ውስጥ የአቶ መለስ ዜናዊ ምክትል የነበሩት አቶ አባይ ወልዱ ሊቀመንበር፣ የኮሚኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል።
የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ።
XS
SM
MD
LG