በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግሥት የወጪ ቅነሳ ፖሊሲ ማኅበራዊ ልማትን ሊጎዳ እንደሚችል ባለሞያዎች ጠቆሙ


 የመንግሥት የወጪ ቅነሳ ፖሊሲ ማኅበራዊ ልማትን ሊጎዳ እንደሚችል ባለሞያዎች ጠቆሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:35 0:00

መንግሥት እየተከተለው ያለው የወጪ ቅነሳ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ፣ ማኅበራዊ ዘርፉን እየጎዳው መኾኑን የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ይገልጻሉ፡፡ ነዳጅን ጨምሮ አብዛኛውን ማኅበረሰብ በሚጠቅሙ ዘርፎች ላይ ሲደረጉ የቆዩ ድጎማዎች መነሣትንም ለአብነት ይጠቅሳሉ

ይህ ፖሊሲ፣ ዓለም አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች በሚያደርጓቸው ግፊቶች መንግሥት ከተገበራቸው የፖሊሲ ለውጦች መካከል አንዱ እንደኾነ የሚናገሩት ባለሞያዎቹ፣ ጋናን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ቢተገበርም ውጤት ማምጣት ያልቻለ ነው፤ ይላሉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት ምንም ዓይነት ሜጋ ፕሮጀክት እንዳልጀመረ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ይደመጣል፡፡ ይህም በወጪ ቅነሳ እና የገንዘብ ፍሰቱን በማስተካከል የዋጋ ንረትን ለመገደብ ያለመ እንደኾነ አመልክቷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ፡፡

XS
SM
MD
LG