ዋሺንግተን ዲሲ —
“አንዳርጋቸውን ልቀቁ” የሚል እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በውጭ ያሉ አንዳንድ የኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ድርጅቶች የአቶ አንዳርጋቸውን ሰንዓ ላይ መያዝ አውግዘው የየመን መንግሥት በአስቸኳይ እንዲለቅቃቸው ጠይቀዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የስለላ ሶፍቴዌት ወይም ስፓይዌር የያዙ መልዕክቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ አንድ የግል የኢንተርኔት ድርጅት ለግንቦት ሰባት መሪዎች ለማድረስ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡
ድርጅቱ መልስ መስጠት አይፈልግም፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ስለአቶ አንዳርጋቸው ሁኔታ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ቃልአቀባዩ ተናግረዋል፡፡
ለተጨማሪና ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡