በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በቡድን ሰባት ስብሰባ መጋበዝ እና ትርጉሙ


ኢትዮጵያ በቡድን ሰባት ስብሰባ መጋበዝ እና ትርጉሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:41 0:00

ኢትዮጵያ በቡድን ሰባት ስብሰባ መጋበዝ እና ትርጉሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በጣሊያኗ ሲቺሊ በሚካሄደው የቡድን ሰባት ሀገሮች ስብሰባ ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸው "የኢትዮጵያ ቦታና ሚዛን ከፍተኛ ደረጃ እያገኘ መሄዱን ያሳያል" ሲሉ ልዩ መልዕክተኛቸው አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በጣሊያኗ ሲቺሊ በሚካሄደው የቡድን ሰባት ሀገሮች ስብሰባ ላይ እንዲገኙ መጋበዛቸው "የኢትዮጵያ ቦታና ሚዛን ከፍተኛ ደረጃ እያገኘ መሄዱን ያሳያል" ሲሉ ልዩ መልዕክተኛቸው አስታወቁ፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዮ መልዕክተኛ አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንዳስረዱት ግብዣው ሃገሪቱ እየተለወጠች መሆኗን ከሚያሳዩ መገለጫዎች አንዱ ነው፡፡

በሌላ በኩል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ልዑክ ብርሃነ ገብረክርስቶስ የሰጡት መግለጫ የተጋነነ ነው ሲሉ የተቃዋሚው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ መልዕክቱን አጣጥለውታል፡፡

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

ፕሮፌሰር በየነ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል "በሙሰኝነትና በአድልዎ የተጨማለቀ፣ ሕዝቡን በእጅጉ ያሳዘነና በዚህም ምክንያት ትልቅ አመፅ የተነሣበት መንግሥት 'ሰላማችን፣ ዴሞክራሲያችን' እያለ ለማውራት የሞራል ብቃት የለውም" ብለዋል፡፡

የመድረኩ መሪ አክለውም "ኢትዮጵያን ‘ታላቅ አድርገናታል’ የሚሉት ነገር ቀልድ ነው፤ ኢትዮጵያ ቀድሞም ታላቅ ሃገር ነበረች" ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኢትዮጵያ በቡድን ሰባት ስብሰባ መጋበዝ እና ትርጉሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:14 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG