በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የድምፃዊ ዘርይኹን ወዳጆ አስክሬን ነገ ዐዲስ አበባ ይገባል


የድምፃዊ ዘርይኹን ወዳጆ አስክሬን ነገ ዐዲስ አበባ ይገባል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:41 0:00

ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ፣ ከዚኽ ዓለም በሞት የተለየው ታዋቂው የአፋን ኦሮሞ ድምፃዊ ዘርይኹን ወዳጆ አስከሬን፣ ነገ ማክሰኞ፣ ሚያዚያ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ማለዳ፣ ሕክምናውን ሲከታተል ከቆየበት ሕንድ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ፤ቤተሰቦቹ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የድምፃዊው ታናሽ እህት ዓለምፀሐይ ወዳጆ ድምፃዊው፣ ለሁለት ወራት ገደማ፣ በሕንድ የሕክምና ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል።

የድምፃዊው አስከሬን፣ ነገ ማክሰኞ፣ ሚያዚያ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ማለዳ፣ ወደ ኢትዮጵያ የሚደርስ እንደኾነና የቀብር ሥነ ሥርዓቱም፣ ረቡዕ፣ ሚያዚያ 18 ቀን በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም፣ ከድምፃዊው ቤተሰቦች ለመረዳት ተችሏል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG