በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘንድሮ 240ሺሕ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ይወስዳሉ


ዘንድሮ 240ሺሕ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ይወስዳሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:24 0:00

በኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት 240 ሺሕ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፣ ከመመረቃቸው በፊት የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ፣ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የኮሚዩኒኬሽንና የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ዓመለወርቅ ሕዝቅኤል ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናውን ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው፤ መውጫ ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ደጋግመው የመፈተን ዕድል እንደሚሰጣቸውም ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል፡፡

በዚኽ ጉዳይ ዙርያ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶ/ር ጌታቸው ጥላሁን በበኩላቸው፣ የመውጫ ፈተናው፣ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል፡፡ ኾኖም፣ ርምጃው ጊዜውን የጠበቀ እንዳልኾነ ተችተው፣ የቅድመ ዝግጅት ክፍተትም ሊያጋጥም እንደሚችል ያላቸውን ሥጋት ጠቁመዋል፡፡

XS
SM
MD
LG