አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ለሃያ ዓመታት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝተው ለመነጋገር ተስማምተዋል።
የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ጉባዔው “ሰላም ለማውረድ ያመቻችል” ሲሉ ዛሬ ለአሶሼትድ ፕሬስ የዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ጊዜና ቦታ ግን ገና እንዳልተወሰነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠቁሟል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ይህን ያስታወቁት በኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልሕ የተመራው የኤርትራ ሉዑካን ቡድን ኢትዮጵያ ያካሄደው የሦስት ቀናት ጉብኝት ካበቃ በኋላ ነው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ