በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢሕአዴግና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦታ ጉዳይ


የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር /ኢህአዴግ/ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሣኔዎችን አሣልፎ ማክሰኞ፤ ነሐሴ 29 ቀን 2004 ዓ.ም ማምሻውን ተጠናቅቋል።

ስብሰባው በተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈት በኋላ ባሁኑ ወቅት «ሀገሪቱን እየመራ ያለው ማነው?» ለሚለው እጅግ አንገብጋቢ ጥያቄ በቂ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ትላንት ማታ ባሣለፋቸው ውሣኔዎች ላይ ግን ይህን አስመልክቶ በግልፅ እና በማያሻማ ቋንቋ የተገለፀ ነገር የለም።

የተባለው፥ “… የግንባሩን ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀ መንበር የመሰየም ጉዳይ የግንባሩ ምክር ቤት ሥልጣን በመሆኑ በመስከረም 2005 የመጀመሪያ ሣምንት በሚካሄደው የምክር ቤቱ ስብሰባ እንዲፈፀም የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ወስኗል …” ነው።

«ዲሞክራሲ በተግባር ፕሮግራም» ይህንኑ መነሻ ያደረገ ዝግጅት አለው። ሰሎሞን ክፍሌ የሕገ መንግሥት ባለሙያ ጋብዞ አወያይቷል።

ዝግጅቱን ያዳምጡ፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG