በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲስ አበባ 500 የኤሌክትሪክ መኪኖች ኃይል መሙያ ጣቢያዎች ሊገነቡ ነው


በአዲስ አበባ 500 የኤሌክትሪክ መኪኖች ኃይል መሙያ ጣቢያዎች ሊገነቡ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:30 0:00

የኢትዮጵያ መንግሥት እየናረ ያለውን የሀገሪቱን የነዳጅ ወጪ ለመቀነስ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ ተሸከርካሪዎችን ለማስገባት ወስኗል፡፡ ይህን ውሳኔ ተከትሎም የገንዘብ ሚኒስቴር ባለፈው መስከረም ወር የኤሌክትሪክ መኪኖች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ፈቅዷል፡፡

በዚህ መሰረት እስካሁን ድረስ 7 ሺህ የኤሌክትሪክ መኪኖች ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ በ 10 ዓመት ውስጥም መንግሥት 152 ሺህ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እንደሚያስገባ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ድኤታ አቶ በረኦ ሓሰን ተናግረዋል፡፡

ካርዲናል ኢንዱስትሪስ የተባለ ኩባንያሞ የመኪኖቹን ባትሪ ለመሙላት የሚያስችሉ በዓመት 500 ጣቢያዎችን ለመገንባት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ጋር መስማማቱን ያስታወቀ ሲሆን ለአሜሪካ ድምፅ ሀሳባቸውን ያጋሩ አንድ አስተያየት ሰጪ፣ የኤሌክትሪክ መኪኖች ለነዳጅ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ በማዳንና የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ ረገድ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

በቴክኖሎጂው ዙርያ የሚነሱ ጥያቄዎችና ስጋቶች እንዳሉም ጠቅሰዋል፡፡

XS
SM
MD
LG