በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫ 2005


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ የአካባቢና የከተማ ምክር ቤት ምርጫ የፊታችን ዕሁድ፤ ሚያዝያ ስድስትና በሣምንቱ ሚያዝያ አሥራ ሦስት 2005 ዓ.ም ይካሄዳል።




please wait

No media source currently available

0:00 0:10:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያ የአካባቢና የከተማ ምክር ቤት ምርጫ የፊታችን ዕሁድ፤ ሚያዝያ ስድስትና በሣምንቱ ሚያዝያ አሥራ ሦስት 2005 ዓ.ም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ረዳት ኃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ በጊዜ ሠሌዳ መሠረት የምርጫው ዝግጅት መጠናቀቁን ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ገልፀዋል።

ባለፈው መጋቢት ሃያ ዘጠኝ ለሕዝቡ በሚኖርበት አካባቢ በምርጫ ጣቢያው የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እነማን እንደሚሆኑ፣ የምርጫ ምልክታቸው ምን እንደሆነ እና መራጩ ሕዝብ ለምርጫው ቀን ምን ይዞ መምጣት እንዳለበት፣ የምርጫ ጣቢያው የት የት እንደሆነ ማብራሪያ መሰጠቱን አስታውሰዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫው የሚያደርጉት በመገናኛ ብዙኃንና ሌሎች ዘዴዎች ቅስቀሣም በጊዜ ሠሌዳው መሠረት ዛሬ መጋቢት 4/2005 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል፡፡

የምርጫው ውጤት ቆጠራው እንደተጠናቀቀ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ እንደሚለጠፍና ውጤቱ እርከኑን ጠብቆ በየደረጃው ተደማምሮ ምርጫ ቦርድ ከደረሰ በኋላ ግንቦት ሁለት 2005 ዓ.ም ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው አስታውቀዋል።

የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ከአዲስ አበባ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG