አዲስ አበባ —
የፊታችን ግንቦት ለሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ በዕጩነት የቀረቡ አባሎቻችን በአንዳንድ አካባቢዎች ቅስቀሳ እንዳያደርጉ እየተከለከሉ ነው ሲል ተቃዋሚው መድረክ ስሞታ አሰምቷል፡፡
በተለይ በወረ ጃርሶ እና በባኮ ጉልህ ችግሮች እንደገጠሙት ገልጿል፡፡
ምርጫ ቦርድ ማስተባበያና ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ በራዲዮና በቴሌቪዥን ለማሠራጨት ያዘጋጃቸው የምርጫ ቅስቀሣ መልዕክቶቹ “ቅድሚያ ምርመራ ተደርጎባቸዋል” ሲል ከስሷል፡፡
አብዛኞቹ ሃሣብን በነፃነት የመግለፅ መብትን በሚፃረር መልኩ ቅድሚያ ምርመራ ተደርጎባቸው በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ውድቅ ሆነውብናል” ብሏል ፓርቲው፡፡
ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ተቋማቱ የሠሩት ሕጋዊ ሥርዓትን የተከተለ ነው ብሏል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
አስተያየቶችን ይዩ (2)
ተጨማሪ አስተያየቶችን ለመመልከት ይጫኑ