አዲስ አበባ - ዋሺንግተን ዲሲ —
በመጭው ግንቦት የሚካሄደው ኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ፤ የመራጮች ምዝገባ ትናንት ተጠናቅቋል።
የተፎካካሪ ፓርቲዎች የምረጡኝ ዘመቻ ዛሬ ተጀምሯል።
በዚህ ምርጫ ላይ ከሚሣተፉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ዕጩዎች መካከል የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት በዕጣ ከዕጩነት መሠረዛቸው ተገልጿል።
ሌሎች ከሁለት መቶ በላይ ዕጩዎች በተለያዩ ሰበብ አስባቦች ከዕጩነት መታገዳቸውን ሊቀ መንበሩ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
ምርጫ ቦርድ አቶ ይልቃል በዕጣ ከውድድር ወጭ መሆናቸውን ገልፆ ሌሎች ከምርጫው ተገለሉ የተባሉት ዕጩዎች “… የሌሎች ፓርቲዎች አባላት እንጂ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አይደሉም…” ብሏል።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጋ ዱፊሳ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ “አቶ ይልቃል ጌትነት የፉክክሩ የተሰናበቱት ግልጽ በሆነ ዕጣ አወጣጥ ነው” ብለዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡