No media source currently available
ለመጭው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የፓርቲዎች ምዝገባ ቀነ ገደብ የሚያበቃው በሦስት ቀናት ውስጥ ቢሆንም እስክዛሬ ማመልከቻ ያስገቡ አሥር ያህል ፓርቲዎች ብቻ መሆናቸውን የምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የአንድ ፓርቲ ማመልከቻ ለተጨማሪ ማጣራት ወደ ፖሊስ መላኩን የቦርዱ የኮምዩኒኬሽንስ አማካሪ ገልፀዋል።