በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢድ አል ፊጥር በድብልቅ ስሜት ተከበረ


የዘንድሮ ኢድ አል ፊጥር በዓለም ዙሪያ ባሉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ትናንት ተከብሮ ውሏል።

በዓሉ በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች መከበሩም ታውቋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በዓሉን ለማክበር የተሰባሰቡ ብዙ ሺህ ሙስሊሞች «መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይግባ፤ የታሠሩ መሪዎቻችንን ይፍታ» የሚል የተቃውሞ ድምፅ ማሰማታቸው ታውቋል።

በዚህም ምክንያት በታላቁ አንዋር መስጊድ ኢማም በሐጂ ጣሃ ሙሃመድ ሊደረግ የነበረ ንግግር መቋረጡ ታውቋል።

ሰሎሞን ክፍሌ ያጠናቀረውን ዘገባ ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG