በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያና ግብፅ ኻርቱም ላይ ሳይስማሙ ተለያዩ


የኅዳሴ ግድብ ማሣያ
የኅዳሴ ግድብ ማሣያ

ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ላይ ባለፈው ቅዳሜና ዕሁድ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ባካሄዱት ስብሳባ ላይ የግብፅ ቡድን ይዞ የቀረበውን “መተማመን ማጎልበቻ መርኅ” የሚል ሰነድ ኢትዮጵያ ሳትቀበል ቀረች፡፡





የናይል ወንዝ ተፋሰስ
የናይል ወንዝ ተፋሰስ

please wait

No media source currently available

0:00 0:21:52 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ላይ ባለፈው ቅዳሜና ዕሁድ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ባካሄዱት ስብሳባ ላይ የግብፅ ቡድን ይዞ የቀረበውን “መተማመን ማጎልበቻ መርኅ” የሚል ሰነድ ኢትዮጵያ ሳትቀበል ቀረች፡፡

ሰነዱ ከያዛቸው ሰባት ነጥቦች መካከል ግብፅ በ1929 እና በ1959 ዓ.ም በነበሯት የናይል ተፋሰስ የራስጌ ሃገሮች ዕውቅና በነፈጉት ስምምነት ላይ የተቀመጠው ድርሻ እንዲጠበቅላት የሚጠይቅ፣ የመረጃ ልውውጥን የሚመለከት፣ ኢትዮጵያ የምትሠራቸውን ሥራዎች ቀድማ እንድታሣውቅ የሚሉ እንደሚገኙባቸው በኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

እነዚያ የቀድሞ ሰነዶች በናይል ተፋሰስ ውስጥ ካለው 84 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ 55.5 ቢሊዮኑን ለግብፅ ብቻ የሚደነግጉ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ - በኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር
አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ - በኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር

በእንዲህ ዓይነቱ “ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው ተግባራት ፍቃድ መጠየቅ የሚያስመስል”፣ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ሃገሮችን የጋራ ጉዳይ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያ እንደማትደራደርና በሃገሮቹ የጋራ ልማት ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ውስጥ የታቀፈ፣ ድርድሩም የተዘጋ መሆኑን አቶ ፈቅአሕመድ አመልክተዋል፡፡

የኅዳሴ ግድብ ግንባታንና አባይ ወንዝን በሚመለከት ዓለምአቀፍ የፍተሻና የክትትል ቡድን ማቋቋምን በተመለከተ ከሦስቱ ሃገሮች የሚውጣጡ ባለሙያዎች ሥራውን የመሥራት ችሎታ አላቸው ብላ ኢትዮጵያ እንደምታምን አቶ ፈቅ አሕመድ ገልፀው ዓለምአቀፍ ቡድን ለመቅጠር ሌላ ዓለምአቀፍ ቡድን ይቋቋም የማልን ሃሣብ ኢትዮጵያ አለመቀበሏን አስረድተዋል፡፡

አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG