አዲስ አበባ —
የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የግብፅ ጉብኝት በታቀደው መሠረት እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
አንዳንድ የግብፅ የፓርላማ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚያ ንግግር እንዳያደርጉ ዘመቻ እያካሄዱ ስለመሆናቸው ተጠይቀው ነው፣ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ይሄንን ያስታወቁት፡፡
በያዝነው የጥር ወር ግብፅን የሚጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከሁለቱ ሀገራት ጉብኝት አንፃር ልዩነቶች እየተንፀባረቁ ባሉበት ወቅት ነው፣ ሱዳንን ጨምሮ በካይሮ የተካሄደው የሦስቱ ሀገራት የውሃ ሚኒስተሮች ስብሰባ፣ የለስምምነት ነው የተጠናቀቀው፡፡
ግብፅ በስብሰባው ያነፀባረቀችው አቋም ያንን ተከትሎ መሪዎቿ የሰጡት አስተያየት ኢትዮጵያን አላስደሰተም፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ