አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ኢዴፓ ለነገ፣ ቅዳሜ፤ ሐምሌ 12/2006 ዓ.ም በመብራት ኃይል አዳራሽ ለማካሄድ ጠርቶት የነበረውን ሕዝባዊ ስብሰባ መሠረዙን አርብ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ስብሰባው የሠረዘው “መንግሥት አባላቶቼን እያዋከበብኝ ስለሆነ ነው” በሚል ምክንያት መሆኑንም ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር ለሕዝባዊ ሰብሰባዉ ፍቀድ ሰጥቶት ለስብሰባዉ እየተዘዋወሩ ጥሪ የሚያደርጉ ቀስቃሽ የድርጅቱ አባላት ታስረው ማምሻውን እንደተፈቱም ድርጅቱ አመልክቷል።
የአዲስ አባባ አስተዳደር ሰለሁኔታው እንዲያስረዳ ለመጠየቅ ዘጋቢአችን እስክንድር ፍሬዉ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
የድርጅቱ ን ፕሬዚደንት ዶክተር ጫኔ ከበደን ያነጋገረው የእስክንድር ፍሬዉ ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፤ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡት፡፡