አዲስ አበባ - ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
ኢትዮጵያ እአአ ከ 2008 አም አንስቶ ማለት በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በፖልዮ ማለትም በልጅነት ልምሻ የተያዘ ሰው እንደተገኘ ማስታወቋን የአሜሪካ ድምጽ ሬደዮ ዘጋቢ ሜሪ አሊስ ሳሊናስ ያነጋገረቻቸው የሮተሪ-ኢንተርናሽናል ፖሊዮን የማጥፋት ዓለምአቀፍ ዘመቻ አባል ካሮል ፓንዳክ መግለፃቸውን ዘግበናል፡፡
የታመችው ያልተከተበች የአንድ ዓመት ተኩል ሕፃን መሆኗን ያስታወቁት ፓንዳክ ሶማልያ ውስጥ አንድ መቶ የሚሆኑ፣ በሰሜን ኬንያ ደግሞ ከአሥር በላይ የሚሆኑ የፖልዮ ህሙማን እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
“አካባቢው ለሶማሊያ ቅርበት ያለው በመሆኑ የቫይረሱ ወደዚያ መዛመት የሚደንቅ አይደለም፡፡ ይህ በኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ ውስጥ የተከሰተው ፖሊዮ በአፍ በሚወሰደው ጠብታ ልንደርስባቸው ያልቻልን ሕፃናት መኖራቸውን ነው፡፡” ብለዋል ፓንዳክ፡፡
ፓንዳክ አክለውም ሶማሊያ ውስጥ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ብዙ ሕፃናትን ለክትባት መድረስ አንዳልተቻለም ጠቁመው ሁኔታው ለቫይረሱ ፈጣን መስፋፋት ምክንያት መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ስለሁኔታው ለአሜሪካ ድምፅ መግለጫ የሰጡት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የክትባት ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ ስንታየሁ አበበ በጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዴኤታው በዶ/ር ከበደ ወርቁ የሚመራ ግብረኃይል ተቋቁሞ ሰሞኑን ጥናት ሲደረግ መሰንበቱን አመልክተዋል፡፡
እንደተባለው አንድም ቢሆን ሕፃን ለፖሊዮ ቫይረስ ተጋልጦ ከተገኘ ብሔራዊ የክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ አቶ ስንታየሁ ጠቁመዋል፡፡
ፖሊዮ ከኢትዮጵያ መጥፋቱ የዛሬ አምስት ዓመት ማለትም በ2000 ዓ.ም በይፋ ተነግሮ እንደነበር ይታወሣል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡