በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በገላን “የማቆያ ጣቢያ” በተላላፊ በሽታ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ኢሰመኮ ገለጸ


በገላን “የማቆያ ጣቢያ” በተላላፊ በሽታ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ኢሰመኮ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:00 0:00

በገላን “የማቆያ ጣቢያ” በተላላፊ በሽታ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ኢሰመኮ ገለጸ

በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ አስተዳደር፣ የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችን ከየቦታው በማንሣት እንዲቆዩ በሚደረጉበት የገላን ክፍለ ከተማ “ማቆያ ጣቢያ” ውስጥ በተከሠተ ተላላፊ በሽታ፣ የሦስት ሰዎች ሕይወት እንዳለፈና 190ዎቹ ደግሞ እንደታመሙ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ፣ ጊዜያዊ የማቆያ ማዕከሉ፣ የተሟላ መሠረተ ልማት የሌለውና ለመቆያ ምቹ እንዳልኾነ ገልጾ፣ ይህም፣ ወደ ጣቢያው የገቡ ሰዎችን ሰብአዊ ክብር በጠበቀ መልኩ ለማስተዳደር አስቸጋሪ አድርጎታል፤ ብሏል፡፡

በኮሚሽኑ የክትትል እና ምርመራ ዲሬክተር ሰላማዊት ግርማይ፣ መግለጫውን አስመልክቶ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፣ ሰዎቹ፣ በማቆያ ጣቢያው የአያያዝ ጉድለት እና ከጎዳና ላይ እንዲነሡ በሚደረጉበት አካሔድ የተነሣ፣ ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተዳርገዋል፤ ብለዋል፡፡ የጎዳና ላይተዳዳሪዎችን ከቦታቸው ለማንሣትና መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ኹሉ፣ መሠረታዊ የሰብአዊ መብታቸው እንዲከበርም፣ ዲሬክተሯ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጊዜያዊ የማቆያ ማዕከሉን “ያስተዳድራል” ከተባለው፣ የዐዲስ አበባ የሴቶች ሕፃናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለዛሬ አልተሳካም፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG