በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ መረጋጋት መኖሩን መንግሥትና መኢአድ ገለፁ


ዳባት ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል፤ አርባ ምንጭ ላይ ሰዎች መታሠራቸውን መኢአድ አስታውቋል፡፡ ወልድያ ላይ እሥረኞች የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡

በምዕራብ አማራ በጎንደርና በደብረ ማርቆስ ሰሞኑን የነበረው ውጥረት በመጠኑ ረገብ ብሏል ያሉት የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ምክትል ፕሬዚዳንት በደቡብ አዳዲስ ችግሮች እየተከሰቱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በክልሉ ውስጥ ያለው የመረጋጋት ሁኔታ የገለፁት የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ “ዛሬ ዳባት ላይ የተደረገው ሰልፍ ሕገ ወጥ ነበር” ብለውታል፡፡

ይሁን እንጂ ሰልፉ ያለ ግጭትና ያለጉዳት መበተኑን ተናግረዋል፡፡

የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጧቸው ማብራሪያዎች ላይ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG