No media source currently available
ሰሞኑን በኦሮምያ ለተከሰተው ችግር መንስዔ የሆኑት በክልሉ ያልተመለሱ ጥያቄዎች፣ ያልተጣጣሙ ፍላጎቶችና የደኅንነት ተግባር መላላት ዋነኞቹ ናቸው ሲሉ የአምቦና ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ፖለቲካል ሳይንስ መምህራን ተናገሩ፡፡ መሰል ችግሮች በክልሉም ሆነ በሀገሪቱ እንዳይፈጠር መንግሥትን ጨምሮ የፖለቲካ፣ የሲቪክና ሃይማኖት ተቋማት ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል፡፡